አዲስ ዘመን አርብ ህዳር 26 ቀን 2018ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐራጅ ቁጥር 08/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ
ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ሸቀጣሸቀጥ
(ልዩ ልዩ እቃዎች) የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ እና Poly(Ethylene Tarphthalate
Plastic cas) ጥሬ ፕላስቲክ፣ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡-
ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር
(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www. auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡በዚህም
መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. ለጨረታ
በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን
ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፤ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ
በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ
ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
2. በተራ
ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
3. ተጫራቾች
የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ
ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን
በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
4. በጨረታው
ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ
ይሆናሉ፡፡
5. በሐራጅ
ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 1 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 331,200፣ ለምድብ 2 ሸቀጣሸቀጥ
(ልዩ ልዩ እቃዎች) ብር 77,800፣ ለምድብ 3 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 1,305,000፣ ለምድብ 4 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች
ብር 28,000 ለምድብ 5 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 193,700 ለምድብ 6 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 12,900፣ ለምድብ
7 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች) ብር 12,000፣ ለምድብ 8 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 768,400፣ ለምድብ 9 ተሽከርካሪ
መለዋወጫዎች ብር 539,000 ለምድብ 10 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 1406,400 ለምድብ 11 ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር
934,000፣ ለምድብ 12 ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 78,500፣ ለምድብ 13 ኤሌክትሮኒክስ ብር 5500፣ ለምድብ 14 ተሸከርካሪ
መለዋወጫዎች 3,700፣ ለምድብ 15 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 187,500፣ ለምድብ 16 አዳዲስ አልባሳት ብር 467500፣
ለምድብ 17 ኮስሞቲክስ ብር 2,200፣ ለምድብ 18 ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 23,60 ለምድብ 19 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች
ብር 44,950፣ ለምድብ 20 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 129,400፣ ለምድብ 21 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 271,800
ለምድብ 22 ኤሌክትሮኒክስ ብር 21,200፣ ለምድብ 23 ኮስሞቲክስ ብር 1,700፣ ለምድብ 24 ኤሌክትሮኒክስ ብር 72,000፣
ለምድብ 25 ኤሌክትሮኒክስ ብር 67,500፣ ለምድብ 26 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 10,800፣ ለምድብ 27 Poly (Ethylens
Torphthalate Pasto res) ጥሬ ፕላስቲክ ብር 67,60ዐ፣ ለምድብ 28 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች) ብር 33,300፣ለምድብ
29 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች) ብር 19,500፣ ለምድብ 30 አዳዲስ አልባሳት ብር 4,000፣ ለምድብ 3 ኤሌክትሮኒክስ ብር
26,300፣ ለምድብ 32 ኮስሞቲክስ ብር 136,000፣ ምድብ 33 ኮስሞቲክስ ብር 10,200፣ ምድብ 34 ኮስሞቲክስ ብር
14,000፣ ምድብ 35 ኮስሞቲክስ ብር 406,400 እና ምድብ 36 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 5,000 በ(Customs
Commission Adama Branch Office) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ
ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡ 6. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ
መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ግቢ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን
ጀምሮ እስከ 6 /ስድስተኛው/ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል፡፡
7. በሐራጅ
ጨረታ እቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
8. አሸናፊ
ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው
ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
9. አሸናፊ
ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ
ይኖርባቸዋል።
10.ለጨረታ
የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
11. ከላይ
በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት
(CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
12. ቅ/ጽ/ቤቱ
የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለጨረታ
ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን አንዳለበት እና የሌላ ባንከ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
NB:- በጨረታ
ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟላ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ለመንግስት ገቢ የምናደርግ እና እቃው በድጋሜ
ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአክሸን ኢትዮጵያን
መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09 05-11 5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት
ይችላሉ፡፡
ተጨማሪ መረጃ፡-
የአዳማ ጉ ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት